የግብፅ ምርጫ እና የተከተለው ተቃውሞ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 21 2004ማስታወቂያ
የአህመድ ሻፊቅ ደግሞ 23,3 ከመቶ የመራጩን ድምፅ በማግኘት የፊታችን ሰኔ አጋማሽ ለሁለተኛ ዙር ምርጫ ይወዳደራሉ። ይህ ይፋ ከተነገረ በኋላ በአሌግዛንድርያ፡ በፖርት ሰይድ፡ በኢዝማይሊያ እና በስዌዝ ከተሞች የኃይል ርምጃ የታከለበት ተቃውሞ ተካሂዶዋል። በተለይ በመዲናይቱ ካይሮ የታህሪር አደባባይ የወጡ ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ተቃዋሚዎች የአህመድ ሻፊቅ የምርጫ ጽሕፈት ቤት ማዕከልን በእሳት አጋይተዋል። በዚሁ ጊዜም ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋ ግጭት ቢፈጠርም፡ ቀደም ሲል የጄዳው ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ በስልክ እንደገለጸልን፡ በወቅቱ ሁኔታው የተረጋጋ ይመስላል።
ነቢዩ ሲራክ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ