የግብፅ መንግሥት የተቃዉሞ ሰልፈኞችን አሰረ
ሰኞ፣ ግንቦት 8 2008ማስታወቂያ
የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች የግብጽ ፍርድ ቤት በጅምላ ሰዎቹ ላይ የሰጠው ፍርድ አግባብ አይደለም ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። 101 ሰዎች እንደ ጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር በ2013 ጸንቶ የነበረውን የጎዳና ሰልፍ ዕገዳ በመተላለፍ በሚል የአምስት ዓመት እሥር ተበይኖባቸዋል ሲል አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። የተቀሩት አምሳ አንዱ ደግሞ የሁለት ዓመት እስራት የተፈረደባቸው የግብጽ መንግሥት በቁጥጥሩ ስር የሚገኙ ሁለት የቀይ ባሕር ደሴቶችን ለሣዑዲ ዓረቢያ ለመስጠት መወሰኑን በመቃወም ሰልፍ በመውጣታቸው እንደሆነ ነዉ የተነገረዉ። ስለ ግብፅ ፍርድ ቤት ብይንና ስለ ግብፅ ወቅታዊ ሁኔታ ኬንያ የሚገኘዉ ወኪላችን በስልክ አነጋግረነው ነበር ።
ከፋሲል ግርማ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዩ ለገሠ