የግብፅ መንግሥት እና የሲና የፀጥታ ሁኔታ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 20 2007ማስታወቂያ
ከአምስት ቀናት በፊት ባነጎደው ቦምብ ቢያንስ 30 የግብፅ ወታደሮችን ገድሎ፣ 30 አቁስሎዋል፣ ሌሎች ታጣቂዎች በአንድ የጦር ኃይሉ መቆጣጠሪያ ኬላም ላይ ተኩስ ከፍተው ሶስት ወታደሮችን ሕይወት አጥፍተዋል። ይህን ተከትሎ የግብፅ ፀጥታ ኃይል ባለሥልጣናትም አካባቢውን በተሳለ መንገድ ለመቆጣጠር አንድ ነፃ ቀጠና ለማቋቋም የወሰኑ ሲሆን፣ በዚሁ አካባቢ የሚገኙት መኖሪያ ቤቶችን ስለሚያፈራርሱ ግብፃውያኑ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ በትናንቱ ዕለት አዘዋል።
ኬርስተን ክኒፕ
ይልማ ኃይለሚካኤል
ተክሌ የኋላ