የግብፁ ፓትርያርክ ቀብር
ማክሰኞ፣ መጋቢት 11 2004ማስታወቂያ
ባለፈዉ ቅዳሜ ያረፉት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስያን ፓትሪያርክ ሼኑዳ ሳልሳዊ ዛሬ በአንድ ጥንታዊ ገዳም ዉስጥ ተቀበሩ።በካይሮዉ የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል በተደረገዉ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት የሐገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፥ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች፥ የዉጪ ሐገራት ባለሥልጣናትና የሐይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል።የሽኝት ፀሎቱን የመሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ጳዉሎስ ናቸዉ።የሰማንያ ሥምንት አመቱ አዛዉንት ሼኑዳ ሳልሳዊ ከግብፅ ሕዝብ አስር-በመቶ የሚሆነዉን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን በጥንቃቄ የመሩ ብልሕ መንፈሳዊ አባት እንደነበሩ ብዙዎች ይናገራሉ።በፓትሪያርኩ ሞት ምክንያት ዛሬ በመላዉ ግብፅ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ ዉሏል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ-ሚካኤል ዘገባ አለዉ።
ይልማ ሐይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ