የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትርና የ«ህዳሴው ግድብ»
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 18 2010ማስታወቂያ
ውጭ ጉዳይ ሚንሥትሩ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የሚያደርጉት ውይይት ለዉጤት እንዲበቃ «ገለልተኛ» ያሉት የዓለም ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል። የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትርን ሐሳብ በተመለከተ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንሥቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለምን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬያቸው ነበር። «የሦስትዮች ብሔራዊ ኮሚቴ ሥራውን አኹንም እንደቀጠለ ነው» ያሉት አቶ መለስ «ይኽ ባለበት ኹኔታ ሌላ የሚታሰብ ነገር የለም» ሲሉ አክለዋል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ