1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግሪክ የብድር ድርድር

ረቡዕ፣ የካቲት 11 2007

የዩሮ ቀውስን ተከትሎ ባለፉት ዓመታት በግሪክ ላይ የተጣለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እና የቁጠባ ርምጃ በቅርቡ ወደ ስልጣን የመጣው አዲሱ የግሪክ መንግሥት እንደማይቀበል አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/1EdN5
Eurogruppe kommt in Brüssel zusammen
ምስል picture alliance/AP Photo/Vanden Wijngaert

በዚህ ምክንያትም አቴንስ ከአበዳሪ የገንዘብ ተቋማት እና ከዩሮ ሸሪፍ ተጠቃሚ ሃገራት ጋር የገባችበት ውዝግብ እስካሁን መፍትሄ አላገኘም። በተለይ ከትናንቱ የዩሮ ዞን የገንዘብ ሚኒስትሮች ስብሰባ በኋላ ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ ሆኗል። ግሪክ በገባችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ውል መሠረት ብድር ካላገኘች ፤ የሀገሪቱ ባንኮች ገንዘብ አይኖራቸውም፤ ጡረታ መከፈል አይቻልም፤ ሌላም ሌላም ችግሮች ሊከተሉ እንደሚችሉ ይገመታል። መፍትሄ ስላላገኘው የግሪክ የብድር ድርድር፤ የገበያው ንጉሴን ዘገባ ከዚህ በታች ያገኛሉ።

ገበያው ንጉሴ

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ