1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግሪክ አፋጣኝ የምርጫ ዝግጅት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 22 2007

የአዉሮጳ የቀዉስ እንብርት በምትባለዉ ግሪክ ከመደበኛዉ የምርጫ ጊዜ ቀደም ብሎ በሚቀጥለዉ የጥር ወር አጋማሽ ላይ ጠቅላላ ምርጫ እንደሚደረግ ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/1EDhv
Präsidentenwahl in Athen gescheitert
ምስል Reuters/Y. Behrakis

ለዚህ ዝግጅትም በዛሬዉ ዕለት መንግሥት የሀገሪቱን ምክር ቤት በትኗል። የግሪክ መንግሥት ሀገሪቱ ከገባችበት የኤኮኖሚ ቀዉስ እንድትወጣ በሚል ከዓለም ዓቀፍ አካላት የቀረበለትን የቁጠባ ስልት ተግባራዊ ለማድረግ መሞከሩ፣ ችግሩን ቀርፎ የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የፈየደዉ ባለመኖሩ ባለፉት ጊዜያት ሀገሪቱ በተቃዉሞ ስትናወጥ ቆይታለች። ስለግሪክ የምርጫ ዝግጅትና ዉስብስብ ችግሮች የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ