በመኪና አደጋ 13 ሞቱ 10 ቆሰሉ
ቅዳሜ፣ ሐምሌ 22 2009ማስታወቂያ
የሰራተኞች ማጓጓዣው 23 ሰዎችን ጭኖ ነበር። የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑን የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የኮምዩንኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አስቴር ተክሌ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። « ከትራፊክ አደጋ ነው እኛም መረጃው የደረሰን። መኪናው ተገልብጦ ይመስለኛል። የተጣራ ነገር የለም። የሰራተኞች ሰርቪስ ነበር። ሰራተኞች ሞተዋል። ወደ ስራ ሲሄዱ የነበሩ ናቸው። »
ከሰባት ዓመት በፊት የተመረቀው የግልገል ጊቤ ሁለት የኃይል ማመንጫ በኦሮሚያ ክልል ከጅማ 80 ኪሜ በስተ ምስራቅ ርቀት ላይ ይገኛል። የኃይል ምንጩ የኦሞ ወንዝ ነው።
ልደት አበበ
እሸቴ በቀለ