1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዳፊ ልጅ ሳይፍ አል-ኢስላም በቁጥጥስ ስር ዋለ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 9 2004

የሊቢያዉ መሪ ሞአመር ጋዳፊ ከተገደሉ ከወር ግድም በኋላ የሰላሳ ዘጠኝ አመቱ ልጃቸዉ ሳይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ ዛሪ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።

https://p.dw.com/p/RxR8
ሳይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ(ከቀኝ ወደ ግራ) ተይዞ በአዉሮፕላን ወደ ዜንታን ከተማ ሲወሰድምስል picture alliance/abaca

አለም አቀፉ ወንጀል መርማሪ ፍርድ ቤት ለፍርድ የሚፈልገዉ ሳይፍ አል- ኢስላም በደቡባዊ ሊቢያ ኦባሪ በተሰኝ ቦታ መያዙን የትሪፑሊዉ የሽግግር መንግስት አረጋግጦአል። በሮይተርስ ዘገባ መሰረት የጋዳፊ ሁለተኛ ልጅ ሳይፍ አል-ኢስላም በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛል። እንደ ሳይፍ አል-ኢስላም የዛሪ ወር ግድም ከኔቶ በወረደ ፈንጂ ቀኝ እጁ በመጎዳቱ እጁ በፋሻ መታሸጉን ዘገባዉ አያይዞ ይጠቅሳል። በሊቢያ የኮነሪል ጋዳፊን ስልጣን ይረከባል የተባለዉ እና በብሪታንያ ትምህርቱን የተከታተለዉ ሳይፍ አል-ኢስላም በሊቢያ ከፍተኛ ስልጣን የነበረዉ እንደ ነበር ይታወሳል። ኔዘርላንድ ዴንሃግ የሚገኘዉ አለማቀፍ ወንጀል መርማሪ ፍርድ ቤት ሳይፍ አል-ኢስላምን ህዝብን በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በመግደል ወንጀል ካለፈዉ ሰኔ ወር መጠናቀቅያ ጀምሮ ለፍርድ ሲፈልገዉ እንደ ነበር የሚታወቅ ነዉ። ሳይፍ አል- ኢስላም ጋዳፊ ዴንሃግ አለም አቀፍ ወንጀለኛ መርማሪ ፍርድ ቤት ከቀረበ እድሜ ይፍታህ እንደሚበየንበት፣ በአገሩ በሊቢያ ለፍርድ ከቀረበ ደግሞ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀዉ ይገመታል።

Saif Al Islam Gaddafi Rede
ምስል picture-alliance/dpa


አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን