1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪዉ ድርጅት ማሳሰብያ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 29 2002

ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት RSF በኢትዮጽያ በአሁኑ ወቅት ለጋዜጠኞች ስራ ተስማሚ ሁኔታ አለመኖሩ እንዳሳሰበዉ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/NIx3

በተጨማሪም በአገሪቱ የምርጫ ሁኔታን ለመዘገብ በወጣዉ የስነ-ምግባር ደንብ ላይ የባለሞያዎች አስተያየት ተጨምሮበት አስፈላጊዉ ማሻሻያ እንዲደረግበት የሚያሳስብ ደብዳቤ ከትናንት በስትያ ረቡዕ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መላኩን አስታዉቋል። ስለደብዳቤዉ ይዘት የድርጅቱን የአፍሪቃ ክፍል ተጠሪን የብራስልሱ ዘጋቢያችን አነጋግሯል።


ገበያዉ ንጉሴ፣

አዜብ ታደሰ
ሸዋዪ ለገሰ