1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኛ ዓለምሠገድ ፈቃደ ሥላሴ ዜና እረፍት

ሰኞ፣ መጋቢት 29 2006

ለበርካታ ዓመታት በራድዮ ጋዜጠኝነትና በአሰልጣኝነት ያገለገለችው ጋዜጠኛ ወይዘሮ ዓለምሠገድ ፈቃደ ሥላሴ ህሩይ አረፈች። ከቀዳሚዎቹ የኢትዮጵያ ሴት ጋዜጠኞች አንዷ የነበረችው ወይዘሮ ዓለምሠገድ በማስታወቂያ ሚኒስቴር፣ በቀድሞው

https://p.dw.com/p/1BdSH
Verwelkte Nelke
ምስል imago/imagebroker

የብሥራተ ወንጌል ራድዮ ጣቢያና በኢትዮጵ ራድዮ ዓለም ዓቀፍ አገልግሎት በእንግሊዘኛ ዜና አቅራቢነትና በፕሮግራም አዘጋጅነት ሠርታለች። ለብሥራተ ወንጌልና በኋላም ለኢትዮጵያ ራድዮ እንዲሁም በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት ወጣት የራድዮ ጋዜጠኞችን ለማሰልጠን የበቃች ታዋቂ የማስ ኮምኒኬሽን ባለሞያ ነበረች። ለኢትዮጵያ ባህልና ቋንቋዎች ትልቅ አክብሮት የነበራት ጋዜጠኛ ዓለምሠገድ የተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች መሥራችና አባልም ነበረች። በእንግሊዘኛ ዜናና ፕሮግራም አቀራረብዋ አድናቆት የሚቸራት ጋዜጠኛ ዓለምሠገድ ሴት ጋዜጠኞችን በማበረታታትና በመደገፍም ትታወቃለች። የጋዜጠኛ ዓለምሠገድ የቀብር ስነሥርዓት ቤተሰብዋና ወዳጅ ዘመዶችዋ እንዲሁም የሙያ ባልደረቦችዋ በተገኙበት ሰኞ መጋቢት 29ቀን 2006ዓ,ም ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባዉ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ሂሩት መለሰ

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ