የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ሊወጣ ነዉ
ዓርብ፣ ሐምሌ 22 2008ማስታወቂያ
ቤቶቹ የሚገኙት በዋናነት በቦሌ እና አቃቅ ክፍለ ከተሞች ሲሆን ኮዬ ፈጬ፣ በቅልንጦ ስሆኑ የካ እና ሃያት በተባሉ ልዩ ስም የሚታወቁ የተለያዩ ፕሮጄክቶች እንዳሉም አቶ ሽሜሊስ ይናገራሉ።
መኖሪያ ቡቶቹን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ስለሚወሰዱት ቅድመ ሁኔታዎች፣ ቀሪዉን 80 ወይም 90 ከመቶዉ ተጠቃሚዎች ቀስ በቀስ እንዲከፍሉ የተደረገበት አሰራር ምን ያህል የገቢ ምንጫቸዉን ያማከለ ነዉ ለሚለዉ ጥያቄ፣ እንድሁም ይህን ዕዳ ወይም ብድር መክፈል ካልቻሉ ሌሎች ኮንዶምንየሞች ላይ እንደሚደረገዉ ለሌላ አካል መሸጥ ይቻል እንደሆነ ላቀረብነው አቶ ሺሜልስ ማብራርያ ሰቶዋል። ለበለጠ መረጃ አዉድዮን ያዳምጡ።
በዚህ ጉዳይ ላይ በዶቼ ቬሌ ድረ ገፅ ላይ ያወያየናቸው አስተያየት ሰጭዎች የከተማዋ አመራሮች የተለያየ መግለጫ ውዥንብር ውስጥ እንዳስገባቸው፣ እነዚህ የጋራ ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላለው ማህበረሰብ የታቀደ ነዉ ቢባልም ፣ አላማውን የሳተ ነው በሚል እቅዱን ተችተዋል።
መርጋ ዮናስ
አረያም ተክሌ