የገንዘብ ቀውስ #ላይ ያተኮረው የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ7 ጥቅምት 2001ዓርብ፣ ጥቅምት 7 2001ከአሜሪካን ተነስቶ አውሮፓ እና እስያን ያዳረሰው የገንዘብ ቀውስ ትናንት ብራሰልስ ቤልጅየም የተከፈተው የሀያ ሰባቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ዋነኛ የመነጋሪያ ርዕስ ነበር ።https://p.dw.com/p/FcHRየህብረቱ ኮሚሽነር ጆሴ ማኑዌል ባሮሶ እና የወቅቱ የህብረቱ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዞምስል APማስታወቂያ በአናት የመጣው የገንዘብ ቀውስ የጉባኤውን ቀልብ ይሳብ እንጂ ከወራት በፊት አስቀድሞ በተያዘው አጀንዳ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመከላከል ከዚህ ቀደም አባላት የተስማሙባቸውን ዝርዝር ነጥቦች ና የአየርላንድ ህዝብ በህዝበ ውሳኔ ውድቅ ያደረገው የተሻሻለው የሊዝበኑ ውል ላይ ለመወያየት ነበር የታቀደው ።