የገና ዋዜማ በቫቲካን
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 15 2007ማስታወቂያ
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ዋና መቀመጫ ቫቲካንና የኢጣሊያዋ ርዕሰ-ከተማ ሮም የገናን በዓል ለማክበር በመፈሳዊዉም በዓለማዊዉ ሥርዓት በሰፊዉ ተዘጋጅተዋል።የሮሙ ወኪላችን ተኽል እግዚ ገብረ እግዚ አብሔር እንደሚለዉ ቫቲካንም ሮምም በየዓመቱ እንደሚደረገዉ ሁሉ በገና ዛፍ ዝንጣፊና በመብራት አሸብርቀዋል።ርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ደግሞ የሐይማኖት መሪዎች፤ ፖለቲከኞችና ዲፕሎማቶች በሚገኙበት ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ቃለ-ቡራኬ ይሰጣሉ።ተኽለእዝጊን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ተኽል እግዚ ገብረ እግዚ አብሔር
ነጋሽ መሐመድ