የገና በዓል አከባበር
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 29 2007ማስታወቂያ
የአዲስ አበባው ወኪላችን ዩሀንስ ገብረእግዚያብሄር በመዲና አዲስ አበባ ዞር ዞር እያለና ወደ ሌላ ከተማም ስልክ በመደወል በዓሉ እንዴት እየተከበረ እንደሆነ አጠያይቋል።
የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል በመዲና በርሊን እና አከባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አነጋግሮአል።
ፓሪስ ከተማ የሚገኙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የበዓል መንፈሱ ቀስ በቀስ እየጠፋባቸው እንደሆነ ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ ባገኙት አጋጣቢ በዓሉን አክብረው እንደሚውሉ ለፓሪሷ ወኪላችን ሐይማኖት ጥሩነህ ገልፀውላታል። በተለይ በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዓሉን እንዴት አከበሩት ሐይማኖት ጥሩነህ ገልፃልናለች።
ሮም የሚገኘው የዶይቸ ቬለ ወኪል ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስም እንዲሁ ፤ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ስደተኞች በዓሉን እንዴት እንደሚያከብሩ ከሮም ዘገባ ልኮልናል።
ሁሉንም ከዚህ በታች በድምፅ ያገኛሉ።
ልደት አበበ / ማንተጋፍቶት ስለሺ