1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገና በዓል አከባበር በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና ጂዳ፣

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 29 2003

ገና በዓመት ውስጥ ከሚከበሩት ዐበይት በዓላት አንዱ ነው። የገና መንፈስ፣ በገሃዳዊው ህይወት ረገድም ፣ ከመለኮታዊው ትርጉም የሚስማማ እንጂ የሚለይ እንዳልሆነ የሃይማኖቱ መምህራን ያስረዳሉ።

https://p.dw.com/p/Qozy
የገና በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው ቦታዎች አንዱ፣ ላሊበላ ነው።ምስል picture-alliance / Bildagentur Huber

ፈጣሪ፤ ሰውን ስለመውደዱ ፣ ሰውም እርስ- በርስ እንዲዋደድ አንዱ ለሌላው በጎ እንዲያስብ፣ በጎ እንዲያደርግ ማለት ነው--። ከመንፈሳዊ የአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ ሌላ፤ ገናን ፣ ሰው፤ በየቤቱ እየደገሠ እንደሚያከብር የታወቀ ቢሆንም፤ የዘንድሮው ግን ያን ያህል የሚያወላዳ እንዳልሆነ፤ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ዘጋቢዎቻችን ጌታቸው ተድላና ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላኩልን ዘገባ ያስረዳል።

ገና ፤ በጂዳ፣ እንዴት እንደተከበረም፣ ነቢዩ ሲራክ ዘግቦልናል።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ