የገና በዓል በአዕምሮ እድገት ዝግመት እንክብካቤ ማዕከል
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 28 2008ማስታወቂያ
የአራት አመት ልጃቸው ጆጆ ከሌሎች ሁሉ የተለየ መሆኑን።በጎርጎሮሳዊው1995 ዓ.ም.በአንድ ቴሌቭዥን ስለ የአዕምሮ እድገት ዝግመት የተዘጋጀ መሰናዶ ከተመለከቱ በኋላ ግን የልጃቸውን ነገር ጠረጠሩ። ከብዙ አመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ወ/ሮ ዘሚ ለልጃቸው አስፈላጊውን ድጋፍና ክብካቤ እንዲያገኝ ማድረግ ቢችሉም በአገሪቱ ያለውን ችግር ሲታዘቡ ማዘናቸው አልቀረም። ኢትዮጵያ እና መሰል ደሐ አገሮች የአዕምሮ እድገት ዝግመት ላይ በቂ የህክምና ማዕከላት የሉም። ወ/ሮ ዘሚ በኢትዮጵያ የኒያ ፋውንዴሽን አዕምሮ እድገት ዝግመት እንክብካቤ ማዕከልን መስርተዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ወደ ማዕከሉ ጎራ ብሎ የገና በዓል አከባበርን ቃኝቷል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሄር
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ