1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጄኔቩ የተ.መ. የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት እና ኢራን

ሰኞ፣ የካቲት 8 2002

የመንግስታቱን ድርጅት 192 አባል ሀገራት የሰብዓዊ መብት ይዞታ በየተራ በየአራት ዓመት አንዴ የሚመረምረው የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ዛሬ የኢራንን የስብዓዊ መብት አያያዝ ፈትሿል ።

https://p.dw.com/p/M1qG

ምዕራባውያን አገራት የቴህራንን አገዛዝ ከተለያየ አቅጣጫ ሲነቅፉ ሩስያ እንዲሁም አንዳንድ የገልልተኛ ሀገራት ንቅናቄና የሙስሊም ሀገራት ማህበር አባላት ደግሞ ለኢራን ድጋፋቸውን ሰጥተዋል ።ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ካለፈው ዓመቱ የኢራን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በኃላ ስለ ተነሳው ብጥብጥ ዓለም ዓቀፍ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ አስተላልፈዋል ። ኢራን ግን ይህን ውድቅ አድርጋለች ።የዶይቼቬለው ፓስካል ሌሽለር ምክር ቤቱ የኢራንን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ከመረመረበት ከጄኔቭ የላከውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

ስካል ሌሽለር /ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ