የጃዝ ሙዚቃ በኢትዮጽያ
ቅዳሜ፣ ግንቦት 22 2001ማስታወቂያ
በአሁኑ ወቅት ባገራችን ቅኝት ተወጥኖ በዘመናዊ የሙዚቃ መሳርያ የሚቀናበረዉ የጃዝ ሙዚቃ ተወዳጅነቱ ላቅ ያለ በመሆን ይነገራል። አንቺ ሆዪ፣ ባቲ፣ ትዝታና፣ አንባሰልን በዘነናዊ ሙዚቃ መጫወቻ በተለይም በዘመናዊዉ ከበሮ ማለት ድራም በማጠናቀሩ ታዋቂ የሆነዉ ወጣት ኢትዮጽያዊ የዛሪዉ የባህል መድረካችን እንግዳ ነዉ። ሌላዉ ዉ የሙዚቃ አዋቂ ሄኖክ ተመስገንም ስለ ኢትዮጽያ ጃዝ ሙዚቃ ያወራናል። ጀርመናዊዉ የሙዚቃ አዋቂ ከኢትዮጽያዉያን የዘመናዊ ሙዚቃ ተጫዋቾች ጋር በጥምር በመስራቱ ደስተኛ መሆኑን ይገልጽልናል ለሁሉም የባህል መድረካችን ጃዝ ሙዚቃ ተወዳጅነቱ ባይከፋም ባህላችንን እያዳበረ ነዉ ወይ የሚለዉን ጥያቄ አንስቶአል። መልካም ቆይታ