የጀርመን ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት ፍፃሜ
ረቡዕ፣ መጋቢት 11 2005ማስታወቂያ
የጀርመን ፕሬዝዳንት ዮአሂም ጋውክ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የ 4 ቀናት ጉብኝት ዛሬ አጠናቀዋል ። በ4 ቀናት የኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር የተነጋገሩት ጋውክ ጀርመን ለኢትዮጵያ ልማት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል ። ሆኖም በኢትዮጵያ በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት አጠባበቅ ረገድ ብዙ መሰራት ያለባቸው ተግባራት እንዳሉ ተናግረዋል ። ጋውክ ዛሬ ከአዲስ አበባ ከመነሳታቸው በፊት የአዲስ አበባውን የተግባረ እድ ትምህርት ጎብኝተዋል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ