የጀርመን የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነት
ዓርብ፣ ጳጉሜን 2 2004ማስታወቂያ
የጀርመን የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነት
ለአንድ ወር የሚዘልቀውን የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነት ባለፈው ቅዳሜ የተረከበችው ጀርመን በመካከለኛው ምሥራቅና በአፍጋኒስታን ላይ ያተኮሩ አብይ ጉባኤዎችን እንደምታዘጋጅ አስታወቀች ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጀርመን አምባሳደር ፔተር ቪቲሽ እንዳሉት መስከረም አጋማሽ ላይ የመንግስታት መሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚካፈሉበት የአረቡ አለም ህዝባዊ አብዮት በመካከለኛው ምሥራቅ ባመጣቸው ለውጦችና በአረብ ሊግ ሚና ላይ የሚያተኩር ጉባኤ ተጠርቷል ። ከዚያ አስቀድሞ ደግሞ በአፍጋኒስታን ከኔቶ መውጣት በኋላ የሚኖረውን የሥልጣን ሽግግር የተመለከተ ልዩ ውይይት ይካሄዳል ። ሆኖም አምባሳደሩ እንዳሉት የሶሪያ ውዝግብ በአጀንዳ አልተያዘም ። ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝር ዘገባ አለው
።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ