1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የቤተሰብ ፖሊሲ

ሐሙስ፣ የካቲት 26 2001

ከአውሮፓ ህብረት አባል አገራት በህዝብ ብዛት ግንባር ቀደሙን ስፍራ የምትይዘው ጀርመን ከሰማንያ ሁለት ሚሊዮን ህዝብ በላይ መኖሪያ ናት ።

https://p.dw.com/p/H6Tv
ምስል AP

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ይህ ቁጥር ከአርባ ዓመት በኃላ በአስር ሚሊዮን ገደማ ቀንሶ ወደ ሰባ ሚሊዮን ማሽቆልቆሉ አይቀርም ። ይህም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ እጅግ የከፋ የምጣኔ ሀብት ድክመት ውስጥ የምትገኘውን ጀርመንን ከሚያሳስቧት ጉዳዮች አንዱ ነው ። በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት የሚወለዱ ህፃናት ቁጥር እየቀነሰ መሄድ አህጉሪቱን ከሚፈታተኗት አሳሳቢ ችግሮች አንዱ እና ምናልባትም ዋነኛው ሳይሆን አይቀርም ። የተወሰኑ አገራት የወሊድ መጠን ባለበት እንዲቀጥል በማድረግ የወደፊቱን አሳሳቢ ችግር ሲከላከሉ ችግሩ የሚያሰጋቸው አንዳንዶቹ ደግሞ ትኩረታቸውን ለውጥ ሊያመጡ ወደሚችሉ ዕርምጃዎች ላይ አድርገዋል ።