የጀርመን የልማት ትብብር ሚኒስቴርና ኢትዮጵያ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 12 2004ማስታወቂያ
እስከ 18 ዓመት ሊያሳስር ይችላል በተባለዉ ክስ ጋዜጠኞቹ በመጪው ሳምንት ብይን ይጠብቃሉ። ከዚህ በተጨማሪ ጠጣሩን የፀረ ሽብር ህግ በመጣስ የተከሰሱ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችም የፍርድ ሂደት እንደቀጠለ ነው። ባለፉት ወራት የመንግሥትን አሠራር በሚነቅፉ ላይ ሲካሄድ የቆየውን መጠነ ሰፊ የመያዝና የማሰር ዘመቻ አስመልክቶ የጀርመን ፌደራል መንግሥት ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታን እንድታሻሽል ጥሪ አቅርቧል። አሁን የጀርመን መንግሥት ለኢትዮጵያ ቃል የገባውን 14 ሚሊዮን ዩሮ የእርዳታ ገንዘብ የሚሰጠውም ይህን ጥሪ ኢትዮጵያ ስትቀበል ብቻ ነው። ሉድገር ሻዶምስኪ እንደዘገበው ተችዎች ይህ የጀርመን መንግሥት ያቀረበው ጥሪ በቂ አይደለም ይላሉ። ዘገባውን ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።
ሂሩት መለሰ
ሸዋየ ለገሰ