1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 24 2009

የኢትዮጵያ መንግሥት የደነገገዉን የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያነሳ እና ከዚሕ ቀደም ቃል የገባዉን ፖለቲካዊ ለዉጥ ገቢር እንዲያደርግ የጀርመን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጠየቁ።

https://p.dw.com/p/2cFLj
Bundesaussenminister Sigmar Gabriel l SPD trifft Hailemariam Desalegn
ምስል Imago

Q&A Gabrel mit der äthiopischen Regierung in Botschaft mit Opposition - MP3-Stereo


ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሲግማር ጋብርኤል ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርም ደሳለኝ ጋር ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ከተነጋገሩ በኋላ እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታ ያላቸዉን ወገኖች ጥያቄ መመለስ አለበት።የኢትዮጵያ ልማት የሚድገዉ በተለይ የዉጪ ባለሐብቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚወርቱት በሐገሪቱ ፍትሐዊ ሥርዓት እና መረጋጋት አለብለዉ ሲያምኑ ነዉ።
«(የኢትዮጵያ መንግሥት) የአስቸኳይ ጊዜዉን አዋጅ እንዲያነሳና ከሁሉም በላይ ፖለቲካዊ ለዉጥ ለማድረግ የገባዉን ቃል ገቢር እንዲያደርግ ጠቅላይ ሚንስትሩን በድጋሚ አጥብቀን ጠይቀናል።በተለይ  ተገፍተናል የሚል ስሜት ያላቸዉ ወገኖች በፖለቲካዉ የመሳተፍ እንድል እንዲኖራቸዉ የተሐድሶ ለዉጥ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ።እርግጥ ነዉ ከዚሕ ቀደም የምጣኔ ሐብት ርዳታ ለማድረግ አስታዉቀናል።ይሁንና መዋዕለ ንዋይ ከዉጪ ወደ ሐገሪቱ የሚፈሰዉ በሐገሪቱ ፍትሐዊ ሥርዓት መኖሩ፤የተረጋጉ ሁኔታዎች መኖራቸዉን ባለሐብቶች ሲያረጋግጡ ነዉ።እዚሕ የመጣነዉም ለዚሕ ነዉ።» የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በተጨማሪ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋርም ተወያይተዋል። ከመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ጋር ስለተካሄደዉ ዉይይት ቦታዉ ላይ የነበረዉን የአዲስ አበባዉን ወኪላችንን በስልክ ጠይቀንዉ ነበር።    

ነጋሽ መሃመድ 

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ