1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ክፍለ-ሐገራት ምርጫና ውጤቱ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 2001

የሰንበቱ ምርጫዎች ውጤት ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በሚካሄደው አገር-አቀፍ የፌደራል ም/ቤት ምርጫ ላይ ከወዲሁ እንደተጠበቀው ብርቱ ተጽዕኖ ማሳደሩ የሚቀር አይመስልም

https://p.dw.com/p/JMsM
የሜርክል ዳግም የመመረጥ ቀነሰ እንጂ አልከሰመምምስል AP

በትናንትናው ዕለት በሶሥት የጀርመን ክፍለ-ሐገራት የተካሄደው የም/ቤት ምርጫ ውጤት በቻንስለር አንጌላ ሜርክል መንግሥታዊ ፓርቲ በክርስቲያን ዴሞክራቶች ሕብረት ላይ ብርቱ ሽንፈትን አስከትሏል። ሕብረቱ በዛርላንድና በቱሪንገን ፍጹም የበላይነቱን ሲያጣ ሳይደፈር የቀረው በሣክሶኒያ ብቻ ነው። በኖርድ-ራይን ዌስትፋሊያ ክፍለ-ሐገር የመዘጋጃ ቤቶች ምርጫም ሕብረቱ በጥቅሉ ቀደምት እንደሆነ ይቀጥል እንጂ በርካታ መስተዳድሮችን ለሶሻል ዴሞክራቶች መልቀቁ ግድ ነው የሆነበት። የሰንበቱ ምርጫዎች ውጤት ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በሚካሄደው አገር-አቀፍ የፌደራል ም/ቤት ምርጫ ላይ ከወዲሁ እንደተጠበቀው ብርቱ ተጽዕኖ ማሳደሩ የሚቀር አይመስልም። ከትናንቱ ምርጫዎች በተለይ ተቃዋሚዎቹ የግራ ፓርቲና አረንጓዴዎች ጠንክረው ሲወጡ አዝማሚያው አገሪቱን የሚያስተዳድረው የታላላቁ ፓርቲዎች ጥምር መንግሥት የሕዝብ ድጋፍን እያጣ መሆኑን የሚያመለክት ነው። በሌላ በኩል ድጋፉ እያቆለቆለ የመጣው የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲም በምርጫው ሂደት መበረታታቱ አልቀረም። ዝርዝሩን ከበርሊን ይልማ ሃ/ሚካኤል

Yilma Hinz/ MM

Negash Mohammed