1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን እጩ ተፎካካሪዎች ክርክር

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 30 2009

በጀርመን ከሦስት ሳምንት በኋላ በሚካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ የሚፎካከሩት መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ መሪ ማርቲን ሹልስ እሁድ ዕለት  በቴሌቪዥን የፊት ለፉት ክርክር አካሂደዋል። ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ክርክሮች አኳያ የሁለቱ ተፎካካሪዎች የፖለቲካ ክርክር ቀዝቃዛ እንደነበር ነዉ አስተያየት ሰጪዎች የጠቆሙት።

https://p.dw.com/p/2jObK
Presseschau TV Duell Bundestagswahl
ምስል FAZ

«ክርክሩ ብዙም የሞቀ አልነበረም»

 አ አር ዴ የተባለው የጀርመን ቴሌቪዥን ባወጣው ጥናት ውጤት መሠረት ሁለቱ ዋነኛ እጩዎች ባካሄዱት በዚሁ ብቸኛው ክርክር ለአራተኛ ጊዜ የሚወዳደሩት የክርስትያን ዴሞክራቶች ኅብረት መሪ ሜርክል ባጠቃላይ አቀረራበቸው የተሻሉ እንደነበሩ ገልጿል። እንዲያም ሆኖ ሁለቱ ተፎካካሪዎች ከሀገር ዉስጥ ጉዳይ ይልቅ በዉጭ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ መምረጣቸዉን ታዛቢዎች ይናገራሉ። አብዛኛዉ ተራ የሀገሪቱ ዜጋም እጅግም የሞቀና ለምርጫ የሚያነቃቃዉ ክርክር እንዳልተደረገ ነዉ አስተያየቱን የሰጠዉ።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ