1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን እርዳታ ለኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 10 2008

የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ለተጠለሉ ስደተኞች የምግብ እርዳታ የሚውል 4.3 ሚሊዮን ዶላር ከጀርመን መንግሥት ሰሞኑን ተቀበለ።

https://p.dw.com/p/1JjFw
Eritrea Mädchen im Flüchtlingslager in der Region Tigrai Äthiopien
ምስል Reuters/T. Negeri

[No title]

የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ለሚገኙ 600,000 ስደተኞች የምግብ ወጪ እና የገንዘብ ድጎማ የሚውል መሆኑን አስታውቋል። ስደተኞቹ ከኤርትራ፤ ደቡብ ሱዳን፤ ሱዳን እና ሶማሊያ የመጡ መሆናቸውንም ገልጧል። የጀርመኑ አምባሳደር ዮዓኺም ሽሚት ለስደተኞች ጉዳይ ጀርመን ከፍተኛ ፖለቲካዊ ትኩረት እንደምትሰጥ ጠቁመዋል። የዓለም የምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጆን አይሌፍ ጀርመን ያደረገችው የገንዘብ ድጋፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሰ