1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን አብራሪ የለሽ የጦር አውሮፕላኖች ፕሮጀክትና ውዝግቡ

ረቡዕ፣ ግንቦት 14 2005

የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር ቶማስ ደሜዜር ባለፈው ሳምንት ይህንኑ ውሳኔ ለጀርመን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሳወቁ ወዲህ አንዳንድ የሃገሪቱ ፖለቲከኞች ፕሮጀክቱ ብዙ ገንዘብ ከፈሰሰበት በኋላ ይቋረጣል በመባሉ ሚኒስትሩን ከመውቀስም አልፈው ከሥልጣን ይውረዱ እያሉ ነው ።

https://p.dw.com/p/18cCb
ምስል picture-alliance/dpa


የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር፣ አብራሪ የለሽ የጦር አውሮፕላኖችን ወይም ድሮን ለመሥራት የጀመረውን ፕሮጀክት እንደሚያቋርጥ ማሳወቁ ማወዛገቡ ቀጥሏል። መንግሥት «ዩሮ ሆክ ሬኮኔሶንስ ድሮን »የተባሉትን ለስለላ ና አመቺ ባልሆኑ ቦታዎች የጠላትን ዒላማ ለማጥቃት የሚውሉትን አብራሪ የለሽ የጦር አውሮፕላኖች ለመሥራት የተያዘውን እቅድ ከሚያቋርጥበት ምክንያት ውስጥ የአውሮፕላኖቹ በረረ የሚጠይቀው ወጪ ከፍተኛ መሆኑ አንዱ እንደሆነ አስታውቋል። የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር ቶማስ ደሜዜር ባለፈው ሳምንት ይህንኑ ውሳኔ ካሳወቁ ወዲህ የሃገሪቱ ፖለቲከኞች ፕሮጀክቱ ብዙ ገንዘብ ከፈሰሰበት በኋላ ይቋረጣል በመባሉ ሚኒስትሩን ከመውቀስም አልፈው ከሥልጣን ይውረዱ እያሉ ነው። ስለ ጀርመን አብራሪ የለሽ የጦር አውሮፕላኖች ፕሮጀክትና ውዝግቡ የበርሊኑን ዘጋቢያችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ ጠይቀናል ።
 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ