1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ህገ መንግስት 60 ኛ ዓመት

ሐሙስ፣ ግንቦት 6 2001

የጀርመን መሰረታዊ ህግ የፀደቀበት ስልሳኛ ዓመት በዚህ ሰሞን ጀርመን ውስጥ በተለያዩ ዝግጅቶች እየታሰበ ነው ።

https://p.dw.com/p/Hqi6
መራሄ መንግስት ኮናርድ አደናወር የዛሬ 60 ዓመት ህገ መንግስቱ ላይ ፊርማቸውን ሲያኖሩምስል picture-alliance/ dpa

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ ከሶሶት ዓመት በኃላ የፀደቀው አንድ መቶ አርባ ስድስት አንቀፆችና አስር ምዕራፎች ያሉት ይኽው ህግ በተለያዩ ጊዚያት ማሻሻያዎች ተደርገውበታል ። ከነዚህም ውስጥ በጎርጎሮሳውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ1956 የጀርመን መከላከያ ሰራዊት በጀርመንኛው አጠራር ቡንደስቬር ሲመሰረት ፣ በ1990 ምዕራብ እና ምስራቅ ጀርመን ሲዋሀዱ ፣ እአአ በ1972 ፣ በ1982 ፣ በ2005 ከመደበኛው የምርጫ ወቅት አስቀድሞ ምርጫ ሲጠራ የተደረጉት ለውጦች ይገኙበታል ። እነዚህን ለውጦች ጨምሮ 53 ያህል ማሻሻያዎች የተደረጉበት ይኽው ህገ እስከዛሬ በጀርመንኛው አጥራር Grundgesetz ወይም መሰረታዊ ህግ ነው የሚባለው የዚህን ምክንያትና ህጉ ከዛሬ ስልሳ ዓመት በፊት ከነበረው የጀርመን ህገ መንግስት የሚለይባቸውን ነጥቦች ፣ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖቹን እንዲሁም አርአያነቱን እስከምን ድረስ እንደሆነ የፍራንክፈርቱን የህግ ባለሞያና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራሸዋን አነጋግሬያቸዋል ። ዶክተር ለማ ከስያሜው ታሪካዊ አመጣጥ ይጀምራሉ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ