የጀርመን ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ብይን
ሐሙስ፣ የካቲት 25 2002ማስታወቂያ
ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናትን ጨምሮ ፖለቲከኞችና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጀርመናውያን የተቃወሙት ይህ የግል ሚስጥር ጥበቃን መብት ይጥሳል የተባለው ህግ ከትናንት በስተያ በመሻሩ ብዙዎች ከመሰለል እፎይታ ያገኙ ያህል ተደስተዋል ። የህጉ ተቃዋሚዎች ያስገቡትን አቤቱታ የመረመረው ፍርድ ቤት ማክሰኞ ባሳለፈው ውሳኔ በህጉ መሰረት እንዲቀመጡ የተደረጉ የስልክ የኢሜልና የኢንተርኔት ግንኙነት መረጃዎች በሙሉ እንዲሰረዙ አዟል ። ይሁንና ብይኑን ጠልቀው የተመለከቱ እንደሚሉት ለፀጥታ ቁጥጥር ሲባል መሰል መረጃዎችን ማስቀመጥና መከታተል ፈፅሞ ይቀራል ማለት አይደለም ። የዛሬው ዝግጅታችን ዓብይ ትኩረት ነው ።
ሂሩት መለሰ ፣ ነጋሽ መሀመድ