የጀርመንና የብራዚል የግማሽ ፍፃሜ ግጥምያ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 1 2006ማስታወቂያ
በግማሽ ፍፃሜው ላቲን አሜሪካዉያኑ ሁለት ሀገራትና ከመሃል አዉሮጳ ሁለት ሀገር ለግጥምያ በመቅረባቸዉ ዉድድሩን ለየት አድርጎታል።
ባለፈዉ ሳምንት መጠናቀቅያ ላይ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለመግባት የተጋጠሙት አርጀንቲና እና ቤልጂየም አንድ- ለባዶ መለያየታቸዉ ይታወሳል ። የአርጀንቲናዉ ጎንዛሎ ሂጎይን ስምተኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ግብ ቡድኑን ወደ ግማሽ ፍፃሜ አድርሶታል። አምስት ሰዓት ላይ የተጋጠሙት ሆላንድና ኮስታሪካ ለግማሽ ፍጻሜዉ መለያ መደበኛ የግጥምያ ሰዓታቸዉን አጠናቀዉ በፍፁም ቅጣት ሆላንድ 4 ለ 3 በማሸነፍ ለቀጣይ ዉድድር ቡድኑን የተቀላቀለዉ። በዚህም በግማሽ ፍፃሜው ላቲን አሜሪካዉያኑ ከአዉሮጳዉያኑ ሀገራት ጋር ይጋጠማሉ። ዛሪ ማክሰኞ ጀርመን ከዓለም ዋንጫ ዉድድር አዘጋጅዋ ከብራዚል፤ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 5 ሰዓት ፤ ነገ ረቡዕ ደግሞ ሆላንድ ከአርጃንቲና ለፍፃሜዉ ለማለፍ ይተናነቃሉ።የብራዚልና የጀርመን ብሄራዊ የእግርኳስ ቡድን እንዴት ይገመገማል በቼክ ሪፐብሊክ የአንድ ከተማ የእግር ኳስ አስልጣኝ የሆኑት ዶክተር ተስፋዬ ጥላሁንን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት አነጋግረናቸዉ ነበር።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ