1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመናዉያን የመረዳዳት ልምድ እና የኢትዮጽያዉያን የበጎ አድራጎት ድርጅት

ሐሙስ፣ ጥር 19 2003

ጀርመናዉያን የተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን በማቋቋም በተለያዩ ክፍለ አለማት የተቸገሩን በመርዳታቸዉ ይታወቃሉ። በተለይ አዲስ አመት መዳረሻ የገና በአል ዋዜማ ጀምሮ የተቸገርን መርዳት የተጠማን ማጠጣት፤ የተራበን ማብላት ባህላቸዉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/Qvxe
ምስል picture-alliance/ dpa

ይህ ባህላቸዉ በተለይ ከሁለተኛ አለም ጦርነት ወዲህ የረዱዋቸዉን ዉለታ ለመመለስ የጀመሩት እንደሆነም ይነገርላቸዋል። በሁለተኛ አለም ጦርነት ወቅት በጀርመን ከፍተኛ ረሃብ እና ችግር እንደ ነበር፣ ጦርነቱን ካበቃ በኳላም ጀርመን በርካታ የምግብ እና የቁሳቁስ እርዳታን ከተለያዩ አገሮች እንዳገኘች ጽሁፎች ያሳያሉ። በዚህም ኢትዮጽያ ስንዴ ቡና እና የብልድ የብርድ ልብስ እርዳታን ማድረስዋ በወቅቱ በጀርመን የነበሩ ጋዜጦች መዘገባቸዉ ይጠቀሳል። ሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ተጠናቆ ጀርመን በእርዳታ አንሰራርታ ህዝቡ የፈራረሰዉን መንገድ እና ህንጻ ጠግኖ በኢንዱስትሪዉም ረገድ ጠንክሮ በመስራት ጦርነቱ ከአለቀ ከሃያ አመት በኳላ በኢኮነሚዉ ረገድ በአለም የሚስተካከላቸዉ አልተገኝም በዚያም ወቅት ነዉ፣ ጀርመናዉያን ዉለታቸዉን ለመመለስ በተለያየ መንገድ የእርዳታ እጃቸዉን መዘርጋት የጀመሩት። እርዳታ በመሰብሰቡ ረገድ በርግጥ በተለይ ቅድምያዉን ቦታ ቤተክርስትያን ይዛ ትገኛለች። ከዝያ በተረፈ በትምህርት ቤቶች የተለያዪ ድርጅቶች እና ተቋማት በየግዜዉ የሚሰበሰበዉ እርዳታ በአገር ዉስጥም ሆነ በሌሎች አገሮች የሚሰጥ ድጎማም ይሆናል። እዚህ በጀርመን በበርሊን ከተማ የሚኖሩ ሰባት ኢትዮጽያዉያን ጀርመናዉያን ላይ ያየነዉን የመርዳት ባህል እኛም በአገራችን አዲስ ህይወት የህጻናት መርጃ ድርጅት በሚል አቋቁመን ልጆቻቸዉን ማሳዳግ ያቃታቸዉን ቤተሰቦች ከቀን ወጭያችን በመቆጠብ በመርዳት ላይ መሆናቸዉን ይገልጻሉ። የአዲስ ህይወት የህጻናት መርጃ ድርጅት ተጠሪ አቶ መስፍን አማረ በጀርመን ሲኖሩ ሃያ አምስት አመት በላይ ሆንዋቸል። ኢትዮጽያዉያን የጀርመናዉያንን ምሳሌ በማየት እኛም ለወንድም እህቶቻችን እርዳታ መስጠት ባህልን ማዳበር ይኖርብናል ሲሉም ይገልጻሉ፣ ሙሉ ጥንቅሩን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
ሸዋዪ ለገሰ