1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶ/ር ፍቅሩ ማሩ አቤቱታ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 9 2007

ዶክተር ፍቅሩ ለሲዊድን ጠቅላይ ሚንስትርና ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በጻፉት ተመሳሳይ ደብዳቤ የኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት እስከፊ በመሆኑ የሲዊድን መንግሥት የዜጋዉን መብት ለማስከበር አስፈላጊዉን ጥረት ማድረግ አለበት።

https://p.dw.com/p/1Fi5A
ምስል DW

[No title]

ኢትዮጵያ ዉስጥ በሙስና ጥርጣሬ የታሠሩት ኢትዮጵያዊ ሲዊድናዊዉ የልብ ቀዶ ሕክምና አዋቂ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ከእስር ቤት እንዲፈቱ የሲዊድን መንግሥት ግፊት ያደርግ ዘንድ ጠየቁ።ዶክተር ፍቅሩ ለሲዊድን ጠቅላይ ሚንስትርና ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በጻፉት ተመሳሳይ ደብዳቤ የኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት እስከፊ በመሆኑ የሲዊድን መንግሥት የዜጋዉን መብት ለማስከበር አስፈላጊዉን ጥረት ማድረግ አለበት።ዶክተሩ በደብዳቤያቸዉ እንደገለጹት የሲዊድን መንግሥት የዜጋዉን መብት ለማስከበር ይሕን ያሕል ጊዜ መፍጀት አልነበረበትም።ዶክተር ፍቅሩ ከታሠሩ ሁለት ዓመታቸዉ ነዉ።የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴዎድሮስ ምሕረቱ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ቴዎድሮስ ምሕረቱ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ