1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶይቸ ቬለ የወጣቶች የውይይት መድረክ

ሰኞ፣ ኅዳር 25 2010

ዶይቸ ቬለ ካለፈው ሳምንት ሐሙስ አንስቶ «77 ከመቶው» በሚል ርዕስ በስድስት የአፍሪቃ ቋንቋዎች  እድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች ላሉ አፍሪቃውያን የውይይት መድረክ ከፍቷል። የአማርኛውም ክፍል እንዲሁ። ምክንያቱም እንደ የዓለም ባንክ መረጃ፣ ከሰሀራ በስተ ደቡብ እድሜው ከ 35 ዓመት በታች የሆነው ህዝብ 77 ከመቶው ያህል ነው ተብሎ ይገመታል።

https://p.dw.com/p/2oirB
DW The 77 Percent (Sendungslogo amharisch)

የዶይቸ ቬለ የወጣት አፍሪቃውያን የውይይት መድረክ

ወጣት አፍሪቃውያን አገራቸውን ለቀው በአደገኛው የባህር ጉዞ እንዲሰደዱ ከሚዳርጓቸው ምክንያቶች ዋንኞቹ ድህነት እና  ስራ አጥነት ናቸው። ዶይቸ ቬለ በተደጋጋሚ በሬዲዮ በቴሌቪዥን እና በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በወጣቱ ስጋት እና ተስፋ ላይ የተለያዩ ወገኞችን አወያይቷል።
በዚህ « 77 ከመቶው » በሚል ርዕስ ስር የሚቀርቡ ዘገባዎች ለወጣቱ የበለጠ ጊዜ ሰጥቶ ወጣቱ ራሱ እንዲናገር እና ከሌሎች ወጣቶች ጋር እንዲወያይ መንገድ ይፈጥራል። ይህም ስኬታማ እንደሆነ ባለፈው ሳምንት የተሰራጩ ዘገባዎች ምላሽ ያሳያል። ከጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር  ዶይቸ ቬለ በአማርኛ ፣ በእንግሊዘኛ፤ በፈረንሳይኛ፣ በሐውሳኛ፣ በኪስዋሂሊኛ እና በፖርቹጊዝኛ ዘገባዎቹን ያቀርባል። የአፍሪቃውያን የወጣቱ የፖለቲካ ተሳትፎም ከእርሶቹ አንዱ ነው። አፍሪቃ ለበርካታ  ዓመታት ስልጣን ላይ ያሉ መሪዎች አሏት። እነዚህ መሪዎች ወጣቱን በሚገባ ይወክሉ ይሆን?  ከላይ በተጠቀሱት ቋንቋዎች የተሰራጩ ዘገባዎች ምላሾች እንደሚያመላክቱት ከሆነ ወጣት አፍሪቃውያኑ የመጪውን ጊዜ ኃላፊነት መረከብ ይፈልጋሉ። ስልጣን ላይ ያሉ መሪዎችም ስልጣኑን ለወጣቱ ትውልድ ቢያሸጋግሩ ይመርጣሉ። «ማንም የሚወክለኝ የለም» ይላል ታንዛኒያዊው ወጣት ኢማኑኤል ቶቢ ። ለዶይቸ ቬለ እንደፃፈው ከሆነ በርካታ ወጣቶች ታንዛኒያ ውስጥ ስራ የላቸውም ለትምህርት የወሰዱትን ብድር መልሰው መክፈልም አልቻሉም። በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊም ለአማርኛው ክፍል በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችም በእድሜ የገፉ እንደሆኑ ነው የገለፀዉ።

ባለፈው ዓመት የአፍሪቃ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ሆነዉ የተመረጡት አልፋ ኮንዴ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የአፍሪቃ ሀገራት በመልካም አስተዳደር ላይ መስራት እንዳለባቸው እና ለወጣቱም አስፈላጊ ነገሮች መሟላት እንዳለባቸው ተናግረዋል። የ 79 ዓመቱ ኮንዴ ላለፉት ሰባት ዓመታት የጊኒ ፕሬዚዳንት ሆነውም በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ራሳቸው ግን ስልጣን መልቀቅ ይገባቸዋል ብለው አያምኑም።«ችግሩ የእድሜ አይደለም። ይልቁንስ ወጣቱ ምን ይፈልጋል የሚለውን ነገር ማወቁ ነው ወሳኙ ነገር። 30 ዓመት ሆኖም ለወጣቱ ምንም የማያደርግ ይኖራል። ሌላው ደግሞ 90 ዓመት ሆኖት ለወጣቱ ብዙ አድርጎ ሊሆን ይችላል። እንደ እኔ እንደ እኔ ክርክሩ አቅጣጫውን የሳተ ነው።»
ይህ ግን በርካታ አፍሪቃውያን የሚስማሙበት አይደለም። «እንደ ኮንዴ አይነት አቋም ያላቸው እና ከ 70 ዓመት በላይ የሆኑ ፖለቲከኞች ጡረታ ቢወጡ ነው የሚሻለው» ትላለች ካሜሮናዊያ ሲሪሉ ታማቾ ለዶይቸ ቬለ በሰጠችው የፁሁፍ አስተያየት።  እንደ ወጣቷ ከሆነ ጊኒ ውስጥ እድሜያቸው ከ 50 ዓመት በታች የሆኑ ብቁ እና የወጣቱን ፈተና ሊቀርፉ የሚችሉ ሰዎች አሉ።
ዶይቸ ቬለ « 77 ከመቶው » በሚል ርዕስ  በሚያቀርባቸው  ዘገባዎቹ  ከዚህ በፊት በትጋት ስደትን የሚመለከቱ ዘገባዎች ላይ እንደሰራው አያይዞ መቀጠል ይፈልጋል። ዶይቸ ቬለ ላለፉት 13 ወራት ከአጋር ጣቢያዎች ጋር በመሆን በስምንት የምዕራብ አፍሪቃ ከተሞች ስለ ስደት ምክንያቶች እና መፍትሔያቸው ላይ  ክርክር አካሂዷል። ይሁንና በሜዲትራንያን በኩል የሚደረጉ ስደተኞች አሁንም አላቆሙም። ስደተኞች በመንገድ ላይ ከሚደርስባቸው ሰቆቃዎች ጎን ለጎን ጉዳዮ የሚመለከታቸው ወጣቶች ሀገራቸው መቆየት እንዲችሉ በትምህርት እና ስራ መስኩ ላይ መሻሻል መደረግ እንዳለበት በተደጋጋሚ አንስተው ተወያይተዋል። በውይይም ላይ የመንግሥት ተወካዮች፤ የሲቪክ ማህበረሰብ እና ሌሎች ምሁሮች ተካፍለዋል። ዶይቸ ቬለ እንደዚህ አይነት ውይይቶች እዚህ አውሮፓ ውስጥ ሳይሆን እዛው ወጣት አፍሪቃውያኑ የሚገኙበት ሀገራቸው እንዲካሄድ መርጧል። ብዙ ክርክር ያስነሳው ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት ጋና ውስጥ የተካሄደው ውይይት ነበር።  300 የሚጠጉ አብዛኛው ወጣቶች የተሳተፉበት ይህ ውይይት ላይ ትልቅ ርዕስ ሆኖ የተነሳው ሊቢያ ውስጥ የሚካሄደው የባሪያ ንግድ ነበር። አብዛኞቹ የውይይቱ የቀጥታ ተካፋዮችም ይሆኑ ውይይቱን በቀጥታ በፌስ ቡክ የተከታተሉ የሚመክሩት ወጣቱ በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመግባት ህይወቱን አደጋ ላይ ከሚጥል ሀገሩ እንዲቆይ እና የቻለውን ያህል ሀገሩን ለማሻሻል እንዲጥር ነው ። 
ዶይቸ ቬለ ወጣቱን የሚመለከቱ የተለያዩ የድምፅና የቪዲዮ ዘገባዎችን ማቅረቡን ይቀጥላል። ተከታተሉን አስተያየታችሁንም አካፍሉን።

Sansibar Wahlen Jugendliche Anhänger CUF
ምስል DW/M. Khelef
Kapstadt Straßenszene Armut
ምስል DW

ልደት አበበ/ማርቲና ሺቪኮቪስኪ

ነጋሽ መሀመድ