የዶክተር መረራ ክስ ሒደት
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 25 2009ማስታወቂያ
በተለያዩ የወንጀል ጭብጦች ተከሰዉ የታሠሩት የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የቀድሞ ሊቀመንበር የዶክተር መረራ ጠበቃ ደንበኛቸዉን መጎብኘትና ማነጋገር እንዲችሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ አዘዘ። ችሎቱ ከዚሕ ቀደም የሕግ ትርጓሜ እንዲሰጥበት ለኢትዮጵያ ፌደሬሽን ምክር ቤት የላከዉ ማስረጃ እስካሁን ድረስ ከምክር ቤቱ እንዳልደረሰዉ አስታዉቃል። የተከሳሽ ጠበቃ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ በትርጓሜ ሰበብ የፍርድ ሒደቱን ማጓተቱ ተከሳሾን እየጎዳ ነዉ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ