1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶቸ ቬለዉ ወኪል ተፈታ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 15 2005

የጋዜጠኞችን መብት በማክበር ቻድ ከአንድ መቶ ሰባ-ዘጠኝ ሐገራት አንድ መቶ-ሃያ አንደኛ ናት።ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ከሃያ ዓመት በፊት በመንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የሰፊ፥ በረሐማዋን፥ አፍሪቃዊት ሐገር ሕዝብ በብረት ጡንቻ እንደደፈጠጡት ነዉ።

https://p.dw.com/p/19UB4
Der Korrespondent des französischen Programms im Tschad, Eric Topona, wurde inhaftiert. Zwei Fotos von ihm (von 2012 im DW-Funkhaus)
ኤሪክ ቶፖናምስል DW

የቻድ መንግሥት ላለፉት አራት ወራት አስሮት የነበረዉ በንጃሚና-ቻድ የዶቸ ቬለ የፈረንሳይኛ ክፍል ወኪል ኤሪክ ቶፖና ተፈታ።ጋዜጠኛ ቶፖና ከእስር ቢለቀቅም በተመሠረተበት የ«ሥም ማጥፋት» ክስ በገደብ ሠወስት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል።ጠበቆቹ ፍርዱ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ አንደሚሟገቱ አስታዉቀዋል።የቻድ መንግሥት ጋዜጠኛ ቶፖናን እንዲለቅ ዶቸ ቬለን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾችና፥ ዲፕሎማቶች ከፍተኛ ግፊት ሲያደረጉ በት ነበር።አሁን ቶፖና በገደብም ቢሆን በመፈታቱ ዶቸ ቬለ መደሰቱን አስታዉቋል። ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ።



ባለፈዉ ሰኞ ንጃሚና ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ኤሪክ ቶፖናን «በሥም ማጥፋት ወንጀል» በገደብ ሰወስት ዓመት እስራት ፈርዶበታል።እስራቱ-በገደብ በመሆኑም ጋዜጠኛዉ ተለቋል።«በገደብ ቢፈረድብኝም» አለ ቶፖና «የመለቀቄን ዜና በታላቅ ደስታ ነዉ የተቀበልኩት።»እያለ እንዲፈታ የታገሉለትን፥ ታስሮ የጠየቁ፥ የረዱትን በተለይ ዶቸ ቬለን አመሰገነ።

«የደገፉኝን በሙሉ አመሰግናለሁ።በተለይ ዶቸ ቬለን እና የረዱኝን የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አካላትን በጣም አመሰግናለሁ።የተደረገልኝ ድጋፍ መንፈሴን አጠናክሮ እስከመጨረሻዉ እንድበረታ ረድቶኛል።»

ኤሪክ ቶፖና በንጃሚና የዶቸ ቬለ ወኪል ብቻ አይደለም።የቻድ ጋዜጠኞች ማሕበር ዋና ፀሐፊም ነዉ።የቻድ መንግሥት ቶፖና፥ ሌሎች ጋዜጠኞችንና የድረ-ገፅ አምደኞችን በማሰሩ ጠንካራ ትችትና ወቀሳ ገጥሞታል።ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ድንበር የለሽ ዘገቢዎች የጋዜጠኞቹን መታሰር «ዘፈቀዳዊ» እና «ለቻድ የፕረስ ነፃነት አስጊ» በማለት አዉግዞት ነበር።የጀርመን ትላልቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዶቸ ቬለም የቻድ መንግሥ ቶፖናን እንዲፈታ አበክረዉ ሲጠይቁ ነበር።

«ከሱ ጋር ተሰቃይተናል።» አሉ፥ በዶቸ ቬለ የአፍሪቃ ክፍል ሐላፊ ክላዉስ ሽቴከር ትናንት «በመፈታቱ እፎይታ ተስምቶናል።» እና አከሉ ሽቴከር «በሱ ላይ የደረሰዉ ብዙ ወኪሎቻችን እና ሥራችን ምን ያሕል የጥቃት ኢላማ እንደሚሆኑ አብነት ነዉ» እያሉ።

በድንበር የለሽ ዘጋቢዎች መመዘኛ መሠረት፥ የጋዜጠኞችን መብት በማክበር ቻድ ከአንድ መቶ ሰባ-ዘጠኝ ሐገራት አንድ መቶ-ሃያ አንደኛ ናት።ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ከሃያ ዓመት በፊት በመንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የሰፊ፥ በረሐማዋን፥ አፍሪቃዊት ሐገር ሕዝብ በብረት ጡንቻ እንደደፈጠጡት ነዉ።

ባለፈዉ ግንቦት እነ ቶፖና ከመታሰራቸዉ በፊት የዴቢ መንግሥት በርካታ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በዘመቻ አስሯል።ቶፖና ራሱ ፖሊስ ጣቢያ የቀረበዉ ለምሥክርነት «ትፈለጋለሕ» ተብሎ ነበር።እዚያ ሲደርስ «ሕገ-መንግሥቱን ጥሰሐል፥ ለሐገር አደገኛ» ፅሑፍ በአምደ-መረብ አሳትምሐል» ተብሎ እዚያዉ ቀረ።

ታሰረ።እስር ቤቱ በሰወሰች የተፋፈገ፥መሠረታዊ ቁሳቁቁስና ፅዳት የሌለዉ ለጤነ አደገኛ ነዉ።ጋዜጠኛዉ በወባም ተለከፈ።ቶፖና ክሱን አልተቀበለዉም።ጠበቆቹም «ሆን ተብሎ የተቀነባበረ እና የፈጠራ» በማለት ተቃወሙት።ኋላ አቃቤ ሕግ የወንጀሉን ጭብት ቀይሮ «ሥም ማጥፋት» በሚል አሻሻሎ፥ ባለፈዉ ሰኞ በገደብ አስፈረደበት።ከጠበቆቹ አንዱ እንዳሉት ግን ጋዜጣኛዉን ሙሉ በሙሉ ነፃ ለማድረግ ይግባኝ ይጠይቃሉ።

«ፍርድ ቤቱ ደንበኛችንን በተመሠረተበት ክስ ጥፋተኛ ነሕ ብሎ በገደብ ሰወስት አመት እስራት ፈርዶበታል።እኛ ተከላካይ ጠበቆች ግን ፍርዱን በመቃወም ይግባኝ ለማለት ተዘጋጅተናል።ደንበኛችን የተከሰሰበትን ወንጀል አለመፈፀሙን የሚያረጋግጥ መከላከያ በማቅረባችን በነፃ መሠናበት ነበረበት። ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ባንድ ወር ጊዜ ዉሳኔ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን።ጠንካራ ጥረታችን ትንሽ እድል ከታከለበት ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድቤት (ደንበኛችንን) በነፃ ያሰናብተዋል ብለን እንጠብቃለን።»

የቶፖና አባት ሴሌስታ ቶፖናም እንደ ልጃቸዉ ሁሉ በልጃቸዉ መፈታት ደስ ብሏቸዋል።እንዲፈታ የረዱ፥ የተባበሩትን ሁሉ አመስግነዋልም።የዚያኑ ያክል ልክ እንደ ልጃቸዉ፥ እንደጠበቆቹ፥ እንደ ባልደረቦቹ ሁሉ የሠራዉ ወንጀል ስለሌላ ሙሉ በሙሉ «ነፃ መሆን አለበት» ባይ ናቸዉ።

ነጋሽ መሐመድ

Der Korrespondent des französischen Programms im Tschad, Eric Topona, wurde inhaftiert. Zwei Fotos von ihm (von 2012 im DW-Funkhaus)
ቶፖናምስል DW
Chad's President Idriss Deby Itno (C) holds hands with General of the Chadian contingent in Mali Oumar Bikimo (L) and second-in-command major and his son Mahamat Idriss Deby Itno (R) during a welcome ceremony, on May 13, 2013, in N'Djamena. Some 700 Chadian soldiers returned home to a heroes' welcome after a bloody campaign fighting Islamic insurgents in northern Mali. AFP PHOTO / STR (Photo credit should read STR/AFP/Getty Images)
ኢድሪስ ዴቢ ከጦር ጄኔራሎቻቸዉ ጋርምስል STR/AFP/Getty Images

ተክሌ የኋላ








ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ