የዶቸ ቨለ ዘጋቢዎችና የሙያ ማሻሻያው ሥልጠና፣
ዓርብ፣ ኅዳር 17 2003ማስታወቂያ
በመሆኑም፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት፣ በተሰጠው የሙያ ማሻሻያ ኮርስ ከተካፈሉት መካከል ከጂዳ ፣ ስዑዲ ዐረቢያና ከአሥመራ፣ ኤርትራ የመጡት የዶቸ ቨለ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች ፣ ነቢዩ ሲራክና ጎይቶም ቢሆን ይገኙበታል። ሥልጠናውን ፤ የቱን ያህል ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኙት ተክሌ የኋላ አነጋግሮአቸዋል።
ዛሬ የሁለት ሳምንቱ ሥልጠና የተደመደመ ሲሆን ፣ ሁለቱም የሩቅ ባልደረቦቻችን በእርካታ መንፈስ ነበረ ወደ እስቱዲያአችን ብቅ ብለው ያጫወቱን። በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ በራይን ወንዝ አካባቢ የጣለውና በየመንገዱ፤ በየመስኩና በየጥሻው የተቆለለውን በረዶ በመስኮት በኩል በማየት እያደነቁም ነው፤ ስለቀሰሙት የሙያ ማሻሻያ ትምህርት የነገሩን ። ነቢዩ ሲራክ፣--
መሳይ መኮንን
ተክሌ የኋላ