የዶርዜ የማንነት ጥያቄ
ሰኞ፣ መጋቢት 29 2006ማስታወቂያ
የጉዳዩ አስተባባሪዎች የብሄረሰቦች መብት በተከበረባት ሀገር የዶርዜ ብሄረሰብ ተጨፍልቋል ባይ ናቸዉ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲህ ያለዉን ጥያቄ ያቀረበዉ ዶርዜ ብቻ ሳይሆን ወደ13 የሚደርሱ ብሄረሰቦች መሆናቸዉን ያመለክታሉ። የማንነት እዉቅና ጥያቄ የሚቀርብለት ጉዳዩ የሚመለከተዉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሣ ተክለብርሃን እንደሚሉት ጥያቄዉ ቢቀርብም ምላሹን ለመስጠት ጥናትና ጊዜ ይጠይቃል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሰ