የድሬዳዋ ዛፎችና ወጣቱ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 10 2003ማስታወቂያ
ዋለልኝ፥-የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ እንጂ-የከተማይቱ ማዘጋጃበት አይደለም።ግን የከተማይቱ ማዘጋጃበት ያልሠራዉን፥ ሊሰራዉ ያልፈለገዉን ወይም ለመስራት ያቃተዉን ወጣቱ ብቻዉን እየሠራ ነዉ።ዋለልኝ እኒያን የድሬዳዋ ዉበት፥ መለያና መታዋቂያ የሆኑን አንጋፋ ዛፎች ለመንከባከብ፥ ጊዜ፥ ጉልበትና ትንሽ ጥሪቱን በሙሉ ለነሱዉ አዉሏል።ዛፎቹ በእንክብካቤ እጦትና በእድሜ መገርጀፍ መክንያት እየተሰባበሩና እየወደቁ ነዉ።የወደፊቱ እይታወቅም ላሁኑ ግን የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር እንደዘገበዉ ዋለልኝ ዋለላቸዉ።
ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሀመድ
ተክሌ የኋላ