1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ጦርነት እና የኢጋድ የማደራደር ሚና

እሑድ፣ ጥር 11 2006

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የገጠሙትን አስከፊ ጦርነት ለማስቆም የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የጀመረዉ የማደራደር ጥረት እስካሁን ተጨባጭ ዉጤት አላመጣም።

https://p.dw.com/p/1AtBD
Konflikt im Südsudan Flüchtlinge 16.01.2014
ምስል Reuters

የኢጋድ አባል የሆነችዉ ዩጋንዳ ያዘመተችዉ ጦር ከፕሬዝዳት ሳልቫኪር ጦር ጋር ሆኖ የሳልቫኪር ተቃዋሚዎችን እየወጋ ነዉ። አዲስ አበባ ላይ የተጀመረዉና የተገታዉ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የተኩስ አቁም ጥረት እንደሚቀጥልና ሁለቱም ወገኖች ለመስማማት መስማማታቸዉን የፈረንሳይ የዜና ወኪል በሳምንቱ መጨረሻ ዘግቦአል። ዩጋንዳ በርስ በርሱ ጦርነት ጣልቃ መግባቷ የኢጋድን የሠላም ጥረት ብቻ ሳይሆን የአካባቢዉን ሠላምም ጨርሶ እንዳያደፈርሰዉ አስግቷል።ሌሎቹ የኢጋድ አባል ሐገራት በተለይ ኢትዮጵያና ኬንያ የዩጋንዳን ጣልቃ ገብነት በቸልታ ማለፋቸዉ ገለልተኝነታቸዉን አጠያያቂ አድርጎታል።የዚህ ሳምንት የዉይይት ዝግጅታችን እነዚህ ጉዳዮችን ይቃኛል።

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ