1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን የነፃነት በዓል

ሐሙስ፣ ሐምሌ 2 2007

ደቡብ ሱዳን ራሷን የቻለች ሀገር ለመሆን ከሱዳን የተነጠለችበት 4ኛ ዓመት የነፃነት ቀን በዓልን በማክበር ላይ ትገኛለች። ከአራት ዓመታት በፊት አብዛናኛው ደቡብ ሱዳናዊ ከሱዳን መነጠሉን ሲመርጥ ሀገሪቱ ዛሬ የተዘፈቀችበት የጦርነት አዙሪት ውስጥ አብሬ እዳክራለሁ በሚል አልነበረም።

https://p.dw.com/p/1Fw0c
Konflikt im Südsudan Flüchtlinge 16.01.2014
ምስል Reuters

[No title]

ዛሬ ግን የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና አማፂያን ከገቡበት ጦርነት መውጣት ተስኗቸው ደቡብ ሱዳናውያን መከራ በመግፋት ላይ ይገኛሉ። ጦርነቱ ነዋሪውን ለቁምስቅል ከመዳረጉም በላይ የበርካቶችን ሕይወት አስገብሯል። በሚሊዮኖችን አሰድዷል፣ በርካታ ሴቶች እንዲደፈሩ መንገድ ከፍቷል። ዛሬ ግን ደቡብ ሱዳን እንደሀገር አራተኛ ዓመት የነፃነት ቀን እያከበረች ትገኛለች። የዶይቸቬለው ዳንኤል ፔልስ የደቡብ ሱዳናውያን መሪዎች የነፃነት በዓል አከባበርን በመተቸት የጻፈውን ሐተታ ይልማ ኃይለሚካኤል እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ