1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ምስረታ መተላለፍ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 10 2008

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር እና የአማጽያን መሪ ሪየክ ማቻር ባለፈው ነሐሴ በደረሱት የሰላም ስምምነት መሰረት፣ በዛሬው ዕለት ሰኞ ሚያዚያ 10፣ 2008 ዓም የሽግግሩ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት መቋቋም ነበረበት።

https://p.dw.com/p/1IXuh
Südsudan Rebellenführer Riek Machar
ምስል Reuters/T. Negeri

[No title]

ከመንግሥት ጋር የተደረሰዉን የሰላም ዉል ተግባራዊ ለማድረግም፣ የሀገሪቱን ምክትል ፕሬዚደንትነት ስልጣን ይይዛሉ የተባሉት እና ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ወደምትገኘው የደቡብ ሱዳን የፓጋክ ከተማ ደርሰዋል የተባሉት የአማጽያን መሪ ማቻር ዛሬ መዲናይቱ ጁባ ገብተው ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ግን ማቻር ጉዟቸውን በ24 ሰዓታት እንዳስተላለፉት ነው የዜና ወኪሎች ያመለከቱት፣ ከብዙ ጊዜ ወዲህ የሚጠበቀው የማቸር ጁባ የመግባት ጉዳይ አሁንም እንደገና ለምን እንደተላለፈ የናይሮቢ ወኪላችንን በስልክ ጠይቀንዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ


አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ