1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን የሰላም ጥረትና ኢጋድ

ረቡዕ፣ ጥር 14 2006

ከኣንድ ወር በላይ ለዘለቀውና ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎች ለሞቱበት የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ውጊያ መፍትሄ ለመሻት ነገ ሐሙስ እዚያው ደቡብ ሱዳን ር/ከተማ ጁባ ውስጥ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የምስራቅ ኣፍሪካ የልማት ቤይነ መንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ አባል ሓገራት መሪዎች ጉባዔ ቢሰረዝም የሰላም ጥረቱ ግን ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ።

https://p.dw.com/p/1AvLg
Südsudan Militär Soldaten ARCHIVBILD 2012
ምስል Getty Images

ሰባት ኃገራትን የሚያስተናብረው ኢጋድ የደቡብ ሱዳንን ጦርነት በሰላም ለማስወገድ የተፋላሚ ኃይላት ተወካዮችን ቢያደራድርም እስከ ኣሁን ግን ድርድሩ ያመጣው ውጤት የለም። ለድርድሩ በተለይም ተፋላሚዎችን የተኩስ ኣቁም ስምምነት ለማፈራረም የተደረገው ጥረት የከሸፈው የፕሬዚደንት ሳልቫኪር መንግስት ያሰራቸውን ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ለመፍታት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው።

Südsudan Kämpfe Riek Maschar ARCHIVBILD 2007
ምስል Al-Haj/AFP/Getty Images

የኢጋድ አባል ሓገራት መሪዎች ነገ ሐሙስ ጁባ ውስጥ ጉባዔ ለመቀመጥ ያቀዱት ድርድሩ ለውጤት የሚበቃበትን ብልኃት ለመፈለግ ነበር። ይሁንና የሰሜን ሱዳን ዜና አገልግሎት ትላንት እንደዘገበው ጉባዔው መሰረዙን ኢጋድ ለሱዳን መንግስት በደብዳቤ ኣስታውቐል። የተሰረዘበት ምክኒያት ግን በግልጽ ኣልተነገረም። በጸጥታ ምክኒያት ነው የሚሉ ወገኖች ባይታጡም የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ቃe አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ እንደሚሉት ግን በጁባ ከቁጥጥር ውጪ የወጣ የጸጥታ ችግር የለም። ጉባዔው የተሰረዘው የኣፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የሚካሄድ በመሆኑ ነው ይላሉ አቶ ጌታቸው ረዳ።

Südsudans Präsident Salva Kiir Mayardit
ምስል Reuters

ኢጋድ ደቡብ ሱዳን የሰፈረውን የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለማጠናከር ማቀዱን አስታውቋል ። አባል ሃገራት ከተስማሙ 5500 ወታደሮችን ለማዝመት አቅደዋል ። እስከ ኣሁን ኬኒያን ጨምሮ ኣንዳንድ የኢጋድ አባል ኃገራት ጦር ለመላክ መስማማታቸውን የገለጹ ሲሆን ከወዲሁ ወደዚያው ዘምተው ኣማጺያኑን በመውጋት ላይ የሚገኙት የኡጋንዳ ወታደሮች በሰላም ኣስከባሪ ጦሩ ውስጥ ይካተቱ እንደሆነ ግን የተገለጸ ነገር የለም።

ከኣንድ ወር በላይ በዘለቀው የደቡብ ሱዳን ብጥብጥ እስከ ኣሁን ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ህዝብ ደግሞ መፈናቀሉ ታውቐል።

ጃፈር ዓሊ
ነጋሽ መሃመድ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ