1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ

ዓርብ፣ ግንቦት 15 2006

በደቡብ ሱዳን የኢጋድ አጣሪና ተቆጣጣሪ ቢሮ የበላይ ሐላፊ አምባሳደር ተፈራ ሻዉል እንዳሉት የኦስሎዉ ጉባኤ ከሠብአዊ ርዳታ በተጨማሪ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሐይላት የተፈራረሙትን የሠላም ዉል ገቢር እንዲያደርጉ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ግፊት ያደረገበትም ነበር

https://p.dw.com/p/1C4iv
የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ
ምስል Reuters

የደቡብ ሱዳን የርስ በርስ ጦርነት ለከፋ ችግር ያጋላጠዉን ሕዝብ ለመርዳታ ኦስሎ-ኖርዌ ዉስጥ ሠሞኑን የተደረገዉ ዓለም አቀፍ የለጋሾች ጉባኤ የሕዝቡን ችግር ለማቃለል የሚረዳ ገንዘብ እንደተዋጣበት አንድ የኢጋድ ባለሥልጣን አስታወቁ።በደቡብ ሱዳን የኢጋድ አጣሪና ተቆጣጣሪ ቢሮ የበላይ ሐላፊ አምባሳደር ተፈራ ሻዉል እንዳሉት የኦስሎዉ ጉባኤ ከሠብአዊ ርዳታ በተጨማሪ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሐይላት የተፈራረሙትን የሠላም ዉል ገቢር እንዲያደርጉ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ግፊት ያደረገበትም ነበር።አምባሳደር ተፈራ እንደሚሉት ደቡብ ሱዳን ዉስጥ አልፎ አልፎ ግጭት ቢኖርም የተፋላሚ ሐይላት የሠላም ስምምነት ገቢር እየሆነ ነዉ።አምባሳደር ተፈራን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በሥልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ