1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ስምምነት

ረቡዕ፣ ሰኔ 4 2006

የኢጋድ አባል ሃገራት መሪዎች ትናንት በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ላይ ከተነጋገሩ በኋላ ማምሻውን ባወጡት መግለጫ መንግሥትና አማፅያን ከዚህ ቀደም የተፈራረሟቸውን ሁለት የተኩስ አቁም ስምምነቶች ባለማክበራቸው ቅር መሰኘታቸውን ሳይገልጹ አላለፉም ።

https://p.dw.com/p/1CGmK
Riek Machar und Salva Kiir
ምስል Ashraf Shalzy/AFP/Getty Images

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት በ60 ቀናት ውስጥ ብሄራዊ የአንድነት የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት መስማማታቸው ተገለፀ ። የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ኢጋድ ዛሬ እንዳስታወቀው የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርና የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችላቸውን ውይይት ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል ። ከዚህ በተጨማሪም በግጭቱ ለተጎዳው ህዝብ የሚለገስው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዳይደናቀፍ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል ። የኢጋድ አባል ሃገራት መሪዎች ትናንት በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ላይ ከተነጋገሩ በኋላ ማምሻውን ባወጡት መግለጫ መንግሥትና አማፅያን ከዚህ ቀደም የተፈራረሟቸውን ሁለት የተኩስ አቁም ስምምነቶች ባለማክበራቸው ቅር መሰኘታቸውን ሳይገልጹ አላለፉም ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ