የደቡብ ሱዳን ቀዉስና ሰባቱ ፖለቲከኞች
ዓርብ፣ የካቲት 7 2006ማስታወቂያ
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት የሳል ቫኪር መንግሥትን ከሥልጣን ለማስወገድ አሲራችኋል በሚል ወንጀል ከታሠሩ የሐገሪቱ የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል በድርድር የተፈቱት ሰባቱ አዲስ አበባ በተያዘዉ ድርድር ላይ ለመካፈል እዚያዉ አዲስ አበባ ናቸዉ። ሰባቱ ፖለቲከኞች እነሱም ሆኑ አሁንም እስር ቤት የሚገኙት አራት ባልደረቦቻቸዉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አድርገዋል የሚለዉን የመንግሥት ዉንጀላ አጥብቀዉ ተቃዉመዉታል።የሰባቱ ፖለቲከኞች ቃል አቀባይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሬዝዳት ሳል ቫኪርን ሐገሪቱን ለዉጪ ሐይሎች አሳልፈዉ ስጥተዋል፤ ከጦርነትም ዶለዋታል በማለት ወቅሰዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ጋዜጣዊ መግለጫውን ተከታትሎት ነበር
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ