1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ሕዝበ ዉሳኔና የአረቦች አቋም

ረቡዕ፣ ጥር 4 2003

በየሐገራቸዉ የመንገንጠል ጥያቄ ያነገቡ የተለያዩ አማፂያን ወይም ሕዝብ ያላቸዉ የአረብ ፖለቲከኞች የሱዳን አስተምሕሮት ለነሱም እንዳይተርፍ ሠግተዋል

https://p.dw.com/p/QrHY
ምስል picture alliance/dpa

የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ካለፈዉ እሁድ ጀምሮ በሚሠጠዉ ድምፅ የግዛቲቱን ነፃነት ያፀድቃል ተብሎ በሰፊዉ እየተጠበቀ ነዉ።በየሐገራቸዉ የመንገንጠል ጥያቄ ያነገቡ የተለያዩ አማፂያን ወይም ሕዝብ ያላቸዉ የአረብ ፖለቲከኞች የሱዳን አስተምሕሮት ለነሱም እንዳይተርፍ ሠግተዋል።የአረብ የፖለቲካ አዋቂዎችና ሙሕራን በበኩላቸዉ እንደሚሉት ሱዳን አሁን ለደረሰችበት ለመድረሷ ከካርቱም አምባገነን ገዢዎች እኩል የግብፅን የመሳሰሉ የአረብ ሐገራት ገዢዎችም ተጠያቂዎች ናቸዉ።እዚያዉ ሱዳንና ዉጪ የሚኖሩ ሱዳናዉያን ሥለ ደቡብ ሱዳን ነፃነት የተመሰቃቀለ ሥሜት ነዉ ያላቸዉ። የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ አጭር ዘገባ አለዉ።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ