የደርግ ዘመን ባለሥልጣናት መፈታት
ረቡዕ፣ መስከረም 24 2004ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት፤ «የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል » ብሎ የከሠሣቸው በደርግ የአገዛዝ ዘመን ከፍተኛ ኀላፊነት ከነበራቸው 23 ባለሥልጣናት መካከል፣16 ቱ ትናንት መፈታታቸው ተገልጿል። ባለሥልጣናቱ የተፈቱት፤ በሃይማኖት ተጠሪዎች ጥረት ነው ተብሏል። የሃይማኖት ሰዎች፤ ከወዲሁ፤ ፍትኅና ርትእ እንዲኖር፤ ትኩረት ሰጥተው መሥራት፤ ሰዎች አላግባብ፤ በግፍ እርምጃ እንዳይታሠሩ ፤ እንዳይገደሉ፤ ማስተማር፤ ዕርቀ-ሰላም እንዲወርድ መጣር ፤ መንፈሳዊ ተልእኮአቸው እንደሚያስገድዳቸው የታወቀ ነው። 20 ዓመት በእሥራት ላይ ከቆዩ በኋላ፤ ስለተፈቱት የደርግ ባለሥልጣናት ፤ ታደሰ እንግዳው የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።