1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደርባ ስሚንቶ ኢንዱስትሪ መመረቅ

ዓርብ፣ የካቲት 2 2004

በ 600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ፤ በሰሜን ሸዋ፤ ደርባ በተባለ አካባቢ የተገነባው የስሚንቶ ኢንዱስትሪ ትናንት በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ተመርቋል። ባለፉት 5 ዓመታት እጅግ በመጨመር በግናባታው ዘርፍ ላይ ብርቱ ተጽእኖ አሳድሮ የነበረውን የሲሚንቶ ዋጋ አዲሱ ኢንዱስትሪ ያረጋጋዋል

https://p.dw.com/p/13yCl
ምስል DW

በ 600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ፤ በሰሜን ሸዋ፤ ደርባ በተባለ አካባቢ የተገነባው የስሚንቶ ኢንዱስትሪ ትናንት በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ተመርቋል። ባለፉት 5 ዓመታት እጅግ በመጨመር በግናባታው ዘርፍ ላይ ብርቱ ተጽእኖ አሳድሮ የነበረውን የሲሚንቶ ዋጋ አዲሱ ኢንዱስትሪ ያረጋጋዋል ፤ በሲሚንቶ ዋጋ መናር ሳቢያ ደከም ብሎ የነበረውን የግንባታ ዘርፍም ያነቃቃዋል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል። የኢትዮጵያ ዐመታዊ የስሚንቶ አቅርቦት ከ 600ሺ ቶን አይበልጥም ነበር ፤ ትናንት የተመረቀው ፤ በሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ተገንብቶ በይፋ ሥራ የጀመረው የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ ይህንን ምርት በ 2,3 ሚሊዮን ቶን ያሳድገዋል ተብሏል።ከሙገርና ሞሰብ የስሚንቶ ፋብሪካዎች ጋር የድርባው ኢንዱስትሪ የስሚንቶን ምርት ወደ 9 ሚሊዮን ቶን ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።

ታደሰ እንግዳው

ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሃመድ