የደራሲው ግጥም እና የእሥራኤል ርምጃ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 1 2004ማስታወቂያ
በሚል ርዕስ ሥር ያወጡት ግጥም እዚህ ጀርመን እና እሥራኤል ውስጥ አሁንም ማከራከር ይዞዋል። ግራስ በግጥማቸው እንዳስቀመጡት፡ ኢራን የአቶም ጦር መሣሪያ ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ለሀገርዋ አደገኛ ነው በሚል እሥራኤል በዚችው ሀገር አንጻር ቀድማ የመከላከል የአቶም ጥቃት ልትሰነዝር የምትችልበት ርምጃ የኢራንን ሕዝብ ሊያጠፋ የሚችል ሥጋት ደቅኖዋል። የጀርመን መንግሥትም እሥራኤል ኅልውናዋን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጥረትዋ ላይ ከጎንዋ መቆሙን ያስታወቀበትንም ድርጊት ግራስ አክለው ነቅፈዋል። ግራስ የአቶም ኃያል መንግሥት ያልዋት እሥራኤል የዓለምን ሰላም ሥጋት ላይ መጣልዋን ነው በግጥማቸው የገለጹት። በዚህም የተነሳ የእሥራኤል ሀገር ውስጥ ሚንስቴር ግራስ ወደሀገርዋ እንዳይገቡ ዕገዳ ጥሎባቸዋል። የእሥራኤል መንግሥት ይህንን ብዙ ታዛቢዎች ጠንካራ ያሉትን ርምጃ ለወሰደበት ምክንያት የሰጠውን ምክንያት እንዲያብራራልን ቀደም ሲል የሀይፋ ወኪላችንን ግርማው አሻግሬን በስልክ ጠይቄዋለሁ።
ግርማው አሻግሬ
አርያም ተክሌ
ተክሌ የኋላ